“ሠራዊቱ ለሕግና ለሞራል የሚገዛ በመሆኑ በሕዝብ ላይ ከመተኮስ መስዋእትነትን መርጧል” የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ

372
“ሠራዊቱ ለሕግና ለሞራል የሚገዛ በመሆኑ በሕዝብ ላይ ከመተኮስ መስዋእትነትን መርጧል” የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 26/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሕግና ለሞራል የሚገዛ በመሆኑ በሕዝብ ላይ ከመተኮስ መስዋእትነትን እንደመረጠ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሕወሃት የሽብር ቡድን ላይ ሕግን ለማስከበር የተሰጠውን ግዳጅ በሚገባ መወጣቱንም ገልጿል።
በዘመቻው የሽብር ቡድኑ ንጹሃንን ሽፋን በማድረግ በከፈተው ጥቃት ብዙ መስዋእትነትን የከፈለ መሆኑን ገልጾ፤ ይህም ሠራዊቱ ለሕዝብ ባለው ውግንና የተከፈለ መስዋእትነት እንደሆነ አመልክቷል።
“የሽብር ቡድኑ እንደለመደው የሐሰት ፕሮፓጋንዳውን በተለያየ መንገድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ስም ለማጥፋት ቢሞክርም ሠራዊቱ ለሕግና ለሞራል የሚገዛ በመሆኑ በሕዝብ ላይ ከመተኮስ መስዋእትነትን መርጧል” ብሏል።
የሽብር ቡድኑ ሠራዊቱ ለሕዝብ የከፈለውን መስዋእትነት እንደሽንፈት ቆጥሮ ለፕሮፓጋንዳ እያዋለው እንደሆነ ጠቅሶ፤ “የመቀሌና የትግራይ ሕዝብ የሠራዊቱን ጨዋነት እና ከአካባቢው የወጣበት መንገድ ያውቃልና በዚህ የሚታለል አይሆንም” ሲል ገልጿል።
የኢትዮጵያን ሕዝብ ደጀን ያደረገ ሠራዊት ሁሌም አሸናፊ እንደሚሆንም አስገንዝቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየደብረ ብርሃን መምህራን ኮሌጅ 1 ሺህ 402 መምህራንን አስመረቀ።
Next articleመምህራን የተማሪዎችን ውጤትና ሥነ ምግባር በማሻሻል ላይ ትኩረት ሊሠጡ እንደሚገባ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አሳሰበ።