የደብረ ብርሃን መምህራን ኮሌጅ 1 ሺህ 402 መምህራንን አስመረቀ።

368
የደብረ ብርሃን መምህራን ኮሌጅ 1 ሺህ 402 መምህራንን አስመረቀ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 26/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 402 ዕጩ መምህራንን በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡
ተመራቂዎቹ በ13 የትምህርት ክፍሎች በማታና በቀን መርሃ ግብር ለ3 ዓመታት የሰለጠኑ ናቸው፡፡
በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን ወይዘሮ ታለፍ ፍትህአወቅ ተመራቂዎች በቆይታችሁ ባገኛችሁት ዕውቀት ማኅበረሰባችሁን ማገልገል ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረ ጻድቅ በበኩላቸው ተመራቂዎች ያገኙትን ዕውቀት ለሥራ ፈጠራ እንዲያውሉት ማሳሰባቸውን ፋብኮ ዘግቧል።
ኮሌጁ ዛሬ ለ17ኛ ጊዜ በዲፕሎማ ካስመረቃቸው 1ሺህ 402 እጩ መምህራን መካከል 52 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleያገባኛል የጤና ኢኒሼቲቭ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተጀመረ፡፡
Next article“ሠራዊቱ ለሕግና ለሞራል የሚገዛ በመሆኑ በሕዝብ ላይ ከመተኮስ መስዋእትነትን መርጧል” የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ