ያገባኛል የጤና ኢኒሼቲቭ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተጀመረ፡፡

112
ያገባኛል የጤና ኢኒሼቲቭ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተጀመረ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 26/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአይ ኬር ወይም ያገባኛል የተሰኘ የጤና መርኃግብር ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ለህክምና አገልግሎት ፈላጊዎች የተቀናጀ ህክምና ለመስጠት የሚያስችል ነው፡፡
መርኀ ግብሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ ሆስፒታሎች የሚተገበር ሲኾን በጤና ሚኒስቴር የተዘጋጀ ነው፡፡ በተመረጡ ሆስፒታሎችም እየተሠራበት ይገኛል። የቅድመ ትግበራ ሥራዎች ተከናውነው በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዛሬ የማስጀመሪያ ዝግጅት ተካሂዷል፡፡
በሆስፒታሉ እየተሠሩ የሚገኙ የመሠረተ ልማት ሥራዎችና የህክምና አገልግሎት አሰጣጥም ተጎብኝቷል፡፡ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳሉት መርኀግብሩ በተመረጡ ሆስፒታሎች የማሻሻያ ሥራ ለማጠናከርና የህክምና አገልግሎት ጥራትን ለማሳደግ ትልቅ አስተዋጽዎ ይኖረዋል።
በመርኀ ግብሩ የጤና ሚኒስትሯን ጨምሮ ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ በዝግጅቱ ማጠቃለያ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ የችግኝ ተከላ መከናወኑን ከሚኒስቴሩ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየሰቆጣ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከ6 መቶ በላይ ሰልጣኞችን አስመረቀ።
Next articleየደብረ ብርሃን መምህራን ኮሌጅ 1 ሺህ 402 መምህራንን አስመረቀ።