
የሰቆጣ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከ6 መቶ በላይ ሰልጣኞችን አስመረቀ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 26/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሰቆጣ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በመደበኛ እና በማታ በዲፕሎማ መርሃ ግብሮች በአማረኛ ፣ በእንግሊዘኛ እና በብሔረሰቡ ቋንቋ በሊኒየር ሞዳሊቲ ፣ በስፔሻሊስት፣ በኔራሊስት፣ በተቀናጀና ሳይንስ የስልጠና መስክ ሲያሰለጥናቸው የነበሩ 642 ተማሪዎችን አስመርቋል።
ከተመረቁት ተማሪዎች ውስጥ 46 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። ኮሌጁ ያስመረቀው በቀን መርሃ ግብር ለ11ኛ እና በማታው ለ9ኛ ጊዜ ነው።
ባለፋት ተከታታይ 10 ዓመታት በዲፕሎማ በአማረኛ ፣በእንግሊዘኛ እና በብሔረሰቡ ቋንቋ በመደበኛ ፣ በማታና በክረምት መርሃ ግብሮችም 8 ሺ 9 መቶ 95 ሰልጣኞችን አስመርቋል።
ዘጋቢ:– ፀጋየ አይናለም – ከሰቆጣ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ