በሶማሌ ክልል በአሸባሪው ሕወሓት አገዛዝ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦች ለማቋቋም የድጋፍ መርኃግብር ተጀመረ።

153
በሶማሌ ክልል በአሸባሪው ሕወሓት አገዛዝ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦች ለማቋቋም የድጋፍ መርኃግብር ተጀመረ።
ባሕር ዳር: ሰኔ 26/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሶማሌ ክልል የቀድሞ አመራሮችና በአሸባሪው ሕወሓት አገዛዝ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦች ለማቋቋም ያለመ የድጋፍ መርኃግብር የማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት በጅግጅጋ ተካሂዷል።
የድጋፍ መርኃግብሩ በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ እና በኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) አባላት በጋራ የሚካሄድ ነው።
የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ በ1983 ዓ.ም ወደ ስልጣን የመጣው አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የብሄር፣ ብሄረሰቦችን መብት በማክበር ዲሞክራሲን እንደሚገነባ ቃል የገባ ቢሆንም በተገላቢጦሽ ብሄር ከብሄር ወንድም ከወንድሙ ጋር እንዲጋጭ በማድረግ ሊያተርፍ ሞክሯል ብለዋል።
“ባለፈው ሥርዓት በክልሉ በደል የፈፀሙ በሕግ ይጠየቃሉ እንጂ ከእነርሱ ጋር መደራደርና በጋራ መሥራት የሚታሰብ አይደለም” ብለዋል።
ለተጎዱ ግለሰቦች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ ባለሀብቶችም የድጋፉ አካል እንዲሆኑ ጠይቀዋል።
የሶማሌ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኢንጅነር መሐመድ ሻሌ በበኩላቸው ባለፈው ሥርዓት በአጠቃላይ በሀገሪቱ መሰል ችግሮች እንደነበሩ ጠቅሰው ፓርቲያቸውም ያለፈውን ሥርዓት በደል በማውገዝ ለለውጥ ከሚሠራ አካል ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
የሀገር ሽማግሌዎች ሰብሳቢ ገራድ ኩልምዬ ገራድ መሐመድ በበኩላቸው መንግሥት ልዩነቶችን ጥበብ በተሞላበት መንገድ በመምራት ባለፈው ሥርዓት በክልሉ ጉዳት ለደረሰባቸው ግለሰቦች ድጋፍ እንዲያደርግ መጠየቃቸውን የዘገበው ኢብኮ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“እኛ ዛሬ የምናስቀምጠው ጡብ የነሱን የነገ ቤት ይገነባል” እሸቱ በቀለ (ዶክተር)
Next articleየሰቆጣ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከ6 መቶ በላይ ሰልጣኞችን አስመረቀ።