
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ 100ኛ የምስረታ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለ100ኛው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ (CPC) የምስረታ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን በራሳቸውና በፕሬዝዳንትነት በሚመሩት የብልጽግና ፓርቲ ስም አስተላልፈዋል።
ከ100 ዓመት በፊት የነበረው ራዕይ በቻይናውያን ሀገሪቱን ለማበልጸግ የተጀመረው ሥራ በጠንካራ እና ከልቡ በሚሠራ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ አመራር አማካኝነት ዛሬ ትክክለኛው መስመር ላይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። በዚሁም በፓርቲው በብስለትና ጠንካራ አመራር ተንሰራፍቶ የነበረውን ድህነትን በመቀስ የቻይናውያን ህይወት በእጅጉ ማሻሻል መቻሉን አንስተዋል። በዚህም የቻይና እድገትና ውጤታማነት በግላቸው መነሳሳትን እንደፈጠረላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የቻይና እድገት ለአፍሪካውያንም በጋራ ማደግ እሳቤን በመፍጠር ተጠቃሽ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጽ ለኮምዩኒስት ፓርቲው የአንድ መቶ ዓመት በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።
በተመሳሳይ የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ለቻይናው ኮምዩኒስት ፓርቲ የምስረታ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ፓርቲው በኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ በማድነቅም እንዲቀጥል እና በቀጣይ በጋራ እንደሚሠሩም አቶ ብናልፍ መግለጻቸውን የዘገበው ኢብኮ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ