
ኢትዮጵያ የተሰረቁ ቅርሶቿን ከኔዘርላንድ ልታስመለስ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ቅርሶቹ ከ15ኛው ክፍለ ዘመን በፊት የነበሩ ሦስት ጥንታዊ መጻሕፍቶችን ያካትታል፡፡ ቅርሶቹ ባለፈው ሳምንት ለሽያጭ ጨረታ ቀርበው ነበር፤ በኔዘርላንድ ዘሄግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጨረታውን ያቀረቡትን አካላት እንዲያቆሙ በመጠየቅ እንዲታገዱ አድርጓል፡፡
ኤምባሲው እንዳለው ጨረታው ታግዷል፤ ቅርሶቹም ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ገልጿል፡፡
በኔዘርላንድ ዘሄግ የኢትዮጵያ አምባሰደር ሚሊዮን ሳሙኤል ቅርሶቹ በመመለሳቸው መደስታቸውን ተናግረዋል፡፡
ቅርሶቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ እየተሠራ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከኤምባሲው የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
በታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ