የኢትዮጵያና ህንድን የኢንዱስትሪ ልማትና የንግድ ግንኙነት ለማጎልበት የሚያስችል ምክክር ተካሄደ፡፡

137

የኢትዮጵያና ህንድን የኢንዱስትሪ ልማትና የንግድ ግንኙነት ለማጎልበት የሚያስችል ምክክር ተካሄደ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያና ህንድን የኢንዱስትሪ ልማትና የንግድ ግንኙነት ለማጎልበት የሚያስችል
ምክክር መካሄዱ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳድር ሮበርት ሸተኪንቶንግ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ህንድና ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማትና የንግድ ግንኙነት ለማጎልበት የሚያስችላቸውን ጉዳዮች አንስተዋል።
አዳዲስ ባለሀብቶችን በመሳብ የሁለቱ ሀገሮች የንግድ ሚዛን ለማሻሻል በሚቻልበት መንገድ መክረዋል፤ ኢትዮጵያ እሴት
የታከለባቸውን እቃዎች ወደ ህንድ በምትልክበት ሁኔታዎች ላይ እንደተወያዩ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“አሸባሪው ሕወሓት በሀገራችን ላይ የደኅንነት ስጋት ኾኖ እንዳይቀጥል ተደምስሷል” ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ
Next article“በክልሉ 75 የሚደርሱ የግብርና ግብዓት እና አገልግሎት ማዕከላት ተቋቁመው አገልግሎት እየሠጡ ነው” የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ