
“አሸባሪው ሕወሓት በሀገራችን ላይ የደኅንነት ስጋት ኾኖ እንዳይቀጥል ተደምስሷል” ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ሕወሓት በኢትዮጵያ ላይ የደኅንነት ስጋት ኾኖ እንዳይቀጥል መደረጉን
የመከላከያ ሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ገለፁ፡፡
ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ከከፍተኛ መኮንኖች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ጁንታው ከሰሜን ዕዝ የዘረፋቸውን የሀገር መጠበቂያ
ትጥቆች ይዞ ለመዋጋት ቢሞክርም በሠራዊቱ ጀግንነትና አይበገሬነት በሦስት ሳምንት ውስጥ የመደበኛ ውጊያ መዋጋት
እንዳይችል አድርጎ ደምስሶታል ብለዋል፡፡
በመደበኛ ውጊያ ተመትቶ የተበታተነው የጁንታው ኃይል በሽምቅ ውጊያ ለመዋጋት ቢሞክርም ሠራዊቱ የጁንታውን አውራ
አመራሮችና ተዋጊዎቹን ከተደበቁበት ዋሻና ጎሬ እየለቃቀመ በመደምሰስ እና ለሕግ በማቅረብ የፈፀመው ግዳጅ የተሳካ
መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የመከላከያ ሠራዊት የጁንታው ቡድን በመደበኛም ይሁን በሽምቅ የመዋጋት አቅም እንዳይኖረው አድርጎ በመደምሰሱ የጥፋት
ኃይሉ አማራጭ ያደረገው የውሸት ፕሮፖጋንዳ በመሥራት ሕዝቡ ውስጥ ገብቶ ሕጻናትንና አዛውንትን ከፊት አስቀድሞ መዋጋትን
መርጧል ነው ያሉት፡፡
የመከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ሕግን ለማስከበር ሰምንት ወር ሲቆይ ሕዝቡ የሰላም ተጠቃሚ እንዲሆንና ሰብዓዊ
አገልግሎቶችና ድጋፎች ለሕዝብ እንዲደርሱ መስዋዕትነትን በመክፈል ጭምር ያገለገለ ቢሆንም ከሕዝቡ የተሰጠው ምላሽ ግን
በተቃራኒው ሆኗል ብለዋል፡፡
“የሕዝቡን ፍላጎት ለማሟላትና የጥሞና ግዜ ለመስጠት መንግሥት በወሰነው ውሳኔ መሰረት ሠራዊቱ መቐለን ለቆ ሲወጣ
በሕዝብ መሃል ተደብቆ የነበረው የጁንታው ኃይል መሃል ከተማ ወጥቶ ጨፈረ እንጂ ከሠራዊታችን ጋር አልተዋጋም፤ የመወጋትም
አቅም የለውም” ነው ያሉት፡፡ መረጃው ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m