ምርጫው ለዴሞክራሲ ባህል መሠረት የጣለ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አስታወቀ፡፡

159

ምርጫው ለዴሞክራሲ ባህል መሠረት የጣለ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 25/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ የተካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ መሠረት የጣለና በአንፃራዊነት ስኬታማ እንደነበረ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አስታወቀ።

ኢሰመጉ በቅድመ ምርጫ፣ በድምፅ መስጫ ዕለትና ድህረ ምርጫ ወቅቶች ያለውን አጠቃላይ ሂደት የታዘበውን አስመልክቶ ቅድመ መግለጫ ሰጥቷል።
ምርጫው በተከናወነባቸው በአብዛኞቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች የጎላ የጸጥታ ችግር አለማጋጠሙን የገለጸው ኢሰመጉ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለሚፈጠሩ ችግሮች ምላሽ የሰጠበት ፍጥነት እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ታዛቢዎች ነፃ ሆነው እንዲታዘቡ መደረጉ በምርጫው የታዩ መልካም አጋጣሚዎች እንደነበሩ በመግለጫው ተገልጿል።

ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ልዩ ምርጫ ጣቢያዎች አለመዘጋጀቱ፣ በምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ የሚደረገው የምርጫ ገለፃና ማብራሪያ ወጥነት የሌለው እንደነበር፣ የድምፅ መስጫ ወረቀት እጥረት ባጋጠመባቸው አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ያለ ምርጫ ቦርድ እውቅና የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች እንዲዘጉ መደረጉ የሚሉት በምርጫው ወቅት ከነበሩ ችግሮች መካከል ይገኙበታል ብሏል።

ይህ ቀዳሚ መግለጫ የተዘጋጅው በሁለቱ የድምፅ መስጫ ቀናት በተሰበሰቡ መረጃዎች ብቻ በመሆኑ በቀጣይ ተጨማሪ መረጃዎች ሲገኙ ሊለወጡ የሚችሉ ጉዳዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አስታውቋል። ዘገባው የኢብኮ ነው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleለቀጣዩ የመኸር ምርት ግብዓት በስፋት ለአርሶ አደሮች ተደራሽ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
Next article“አሸባሪው ሕወሓት በሀገራችን ላይ የደኅንነት ስጋት ኾኖ እንዳይቀጥል ተደምስሷል” ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ