
ለቀጣዩ የመኸር ምርት ግብዓት በስፋት ለአርሶ አደሮች ተደራሽ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 25/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የ2013/14 ዓ.ም ለቀጣዩ የመኸር ምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ፣ በየምርጥ ዘር፣ የኬሚካልና የግብርና ኖራ ግብዓቶች በስፋት ለአርሶ አደሩ ተደራሽ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የግብርና ግብዓትና ግብይት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መንግሥቱ ተስፋ እንዳስታወቁት፣ በዘንድሮው ምርት ዘመን የአርሶ አደሩን ፍላጎት ለማሟላት ከ2012 ሐምሌና ነሐሴ ወራት ጀምሮ የአፈር ማዳበሪያ፣ ሸየምርጥ ዘር፣ የኬሚካልና የግብርና ኖራ ግብዓቶች ግዢ 1መቶ በመቶ ተፈጽሞ በስፋት ተደራሽ እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል።
በምርት ዘመኑ በአርሶ አደሩ ፍላጎት መሰረት ለማቅረብ ከታቀደው 18 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል አራት ዓይነት የአፈር ማዳበሪያ ከዩሪያ ውጪ ያለው 15 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል ወይም 85 በመቶው ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ ላይ ደርሷል። ከደረሰው 14 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታሉን ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማጓጓዙን አስታውቀዋል ።
አፈጻጸሙ የዓመታዊ ዕቅዳችንን 85 በመቶ፤ ጅቡቲ ወደብ የደረሰውን በማጓጓዝ በኩል ደግሞ 94 በመቶ ያሳካ ነው ያሉት አቶ መንግስቱ ፣17 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል በመጋዘን የነበሩ የተለያየ ዓይነትና መጠን ያላቸው የአፈር ማዳበሪያ መኖራቸውን አመልክተዋል። ዘገባው የኢፕድ ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ