ባለፉት አስራ እንድ ወራት ከዲያስፓራው በድጋፍ መልክ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር መገኘቱን የኢትዮጵያ ዲያስፓራ ኤጀንሲ አስታወቀ።

293

ባለፉት አስራ እንድ ወራት ከዲያስፓራው በድጋፍ መልክ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር መገኘቱን የኢትዮጵያ ዲያስፓራ ኤጀንሲ
አስታወቀ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 24/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የ2013 በጀት ዓመት በውጤት የታጀቡ የንቅናቄ መድረኮች የተካሄዱበት ጊዜ መሆኑን
የኢትዮጵያ ዲያስፓራ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡
ኤጀንሲው የ2013 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸሙን በገመገመበት ወቅት እንደተጠቀሰው፤ በበጀት ዓመቱ በሀገራዊ ፕሮጀክቶችና
በፐብሊክ ዲፕሎማሲ ላይ የንቅናቄ መድረኮች ተካሂደዋል፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ላይ የ2013 በጀት ዓመት ለተቋሙ ብዙ ምቹ ሁኔታዎች የተፈጠሩበት
መሆኑን ጠቅሰዋል። ዲያስፓራ የሚስተናገድበትን ሁኔታ ማዘመንና ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የተቻለበት ዓመት
እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡ ይህን ተከትሎም በበጀት ዓመቱ ውጤታማ አፈጻጸም ማስመዘገብ ተችሏል ብለዋል፡፡
የኤጀንሲው የፕላኒግና ሞኒተሪንግ ኀላፊ ተስፋዬ ደሜ በበኩላቸው፤ ለታላቁ ሀዳሴ ግድብ በ192 ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር፤
ለገበታ ለሀገር ወደ 30 ሚሊዮን ብር፣ ለኮሮናቫይረስ መከላከል 282 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር፣ ለመከላከያና መልሶ ማቋቋም 600
ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል ብለዋል።
ለበጎ አድራጎት ሥራም ወደ 103 ሚሊየን ብር በዚህ ዓመት ብቻ መሰብሰቡን አብራርተዋል፡፡
በአጠቃላይ ባለፉት አስራ እንድ ወራት ከዲያስፓራው በድጋፍ መልክ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ባለፉት አስራ አንድ ወራት ከዲያስፓራው በሪሚታንስ መልክ ሶስት ቢሊየን ዶላር ተገኝቷል፡፡ የውጭ ጣልቃ ገብነት
ለመካለከል ሰፊ ሥራ ተሰርቶ ደጋፊ አመለካከት መፍጠር የተቻለበት ጊዜ እንደነበርም መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleኢትዮጵያ ተግባራዊ ያደረገችው የተናጠል የተኩስ አቁም አዋጅ ተሰፋ ሰጪ እርምጃ ነው ስትል ሩሲያ አስታወቀች፡፡
Next articleለቀጣዩ የመኸር ምርት ግብዓት በስፋት ለአርሶ አደሮች ተደራሽ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።