
ኢትዮጵያ ተግባራዊ ያደረገችው የተናጠል የተኩስ አቁም አዋጅ ተሰፋ ሰጪ እርምጃ ነው ስትል ሩሲያ አስታወቀች፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 24/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ በትግራይ ክልል ተግባራዊ ያደረገው የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ በክልሉ ላይ ለውጥ ለማምጣት ተሰፋ ሰጪ እርምጃ መሆኑን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሩሲያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ቫሲሊ ኔቤንዚያ ገለጹ፡፡
አምባሳደሩ በሰጡት ወርሃዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በክልሉ እያደረገ ላለው ከፍተኛ የሰብዓዊ ድጋፍ እውቅና ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
ሌሎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማትም ድጋፍ ሊያደርጉ የሚችሉበት መንገድ ሊመቻቻልቸው እንደሚገባ አምባሳደሩ በዚሁ መግለጫቸው ላይ አስታውቀዋል። ዘገባው የኢፕድ ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ