
በትግራይ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ለማስወጣት እየተሠራ ነው።
ባሕር ዳር: ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በትግራይ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ለማስወጣት እየተሠራ መሆኑን የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወይዘሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል እንደተናገሩት ሚኒስቴሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመምከር ተማሪዎቹን ለማስወጣት ትራንስፖርት እያመቻቸ ይገኛል።
ተማሪዎቹ ደኅንነታቸው ተጠብቆ እንዲወጡ ተገቢው ዝግጅት እየተደረገና ሁኔታዎችን እያመቻቸ ይገኛል ነው ያሉት።
ወላጆችም በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚወጡ ሐሰተኛ መረጃዎች ሳይረብሿቸው እንዲጠባበቁ ወይዘሮ አመለወርቅ መጠየቃቸውን ፋብኮ ዘግቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ