
በ2013 በጀት ዓመት እስከ ሰኔ 19 /2013 ዓ.ም ድረስ ከ 18 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 24/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2013 በጀት ዓመት 20 ነጥብ 56 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እስከ ሰኔ 19 /2013 ዓ.ም ድረስ 18 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የቢሮው ኃላፊ ብዙአየሁ ቢያዝን ገልጸዋል።
የገቢ አፈፃፀሙ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ6 ቢሊዮን ብር ብልጫ ማሳየቱን ጠቅሰዋል፡፡
ለተሰበሰበው መልካም የሚባል ገቢ አፈፃፀም የክልሉ አመራር ለገቢ ተቋሙ ያደረገው ድጋፍ፣ የተቋሙ የሥራ ኀላፊዎችና ሠራተኞች ቅንጅት፣ የክልሉ አጋርና ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ኃላፊነት መወጣት፣ የንግድ ዘርፍ ማኅበራት እና የታክስ አምባሳደሮች ያደረጉት ድጋፍ፣ የጋራ ገቢ ቀመር መሻሻል እና ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር ተቀናጅቶ መሥራቱ የጎላ ድርሻ እንደነበረው መግለጻቸውን ከክልሉ ገቢዎች ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ