
ወይዘሮ ኢትዮጵያ ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ 2 ሺህ ዶላር ለገሱ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 24/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ መሪላንድ ያደረጉት ትውልደ ኢትዮጵያዊ ወይዘሮ ኢትዮጵያ አልፍሬድ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ኩራት እንደሚሠማቸው በተደጋጋሚ የሚገልጹት ወይዘሮ ኢትዮጵያ ለህዳሴ ግድቡ ድጋፍ ያደረጉበትን የ2 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ቼክ በስጦታ መልክ አስረክበዋል፡፡ ይሕም አሁን ባለው የዶላር መሸጫ ዋጋ ወደ ኢትዮጵያ ሲመነዘር ወደ 89 ሺህ ብር ገደማ ይሆናል፡፡
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳስታወቁት ወይዘሮ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያውያን በጨዋ ደንብ ምርጫ በማከናወናቸው የተሰማቸውን ኩራትና ደስታም ገልጸዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ