የኮሎኔል ዕምሩ ወንዴ የቀብር ሥነ ሥረዓት ከፍተኛ የመንግሥት ኀላፊዎች፣ አርበኞች እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ቤተክርስቲያን እየተከናወነ ነው።

173
የኮሎኔል ዕምሩ ወንዴ የቀብር ሥነ ሥረዓት ከፍተኛ የመንግሥት ኀላፊዎች፣ አርበኞች እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ቤተክርስቲያን እየተከናወነ ነው።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 24/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) ተወልደዉ ያደጉት በበጌ ምድር ደብረ ታቦር አዉራጃ ሲሆን በልጅነታቸው በቤተ ክርስቲያን የዜማ ትምህርት ተምረዋል። የክቡር ዘበኛ የጦር መኮነን የባህር ኀይል መሥራች እና ምክትል አዛዥ በመሆንም አገልግለዋል።
በኮሪያና ኮንጎ በመዝመትና የዘመቻዉ መሪ በመሆንም ተሳትፈዋል። ኮሎኔል ዕምሩ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ የበኩላቸዉን በመወጣት ሀገርን አገልግለዋል።
ኮሎኔል ዕምሩ ባደረባቸዉ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ ሰኔ 23/2013 ዓ.ም ህይወታቸዉ አልፏል። ዛሬ በቅድስት ካቴደራል ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ አርበኞች፤ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ቤተሰቦቻቸዉ በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል።
ዘጋቢ:– ኤልሳ ጉዑሽ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ያላትን ክብር የሚመጥን ውጤት ለማስመዝገብ ጠንካራ ዝግጅት ተደርጓል” የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ
Next articleበተያዘው ክረምት ከ14 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የፍራፍሬ ችግኝ ለአርሶ አደሮች ለማሰራጨት እየሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡