
ኢትዮጵያ እና እስራኤል የኮሮናቫይረስ ክትባትን በጋራ ሊያመርቱ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 24/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እና እስራኤል የኮሮናቫይረስ ክትባትን በጋራ በኢትዮጵያ ሊያመርቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ፣ ምክትል አምባሳደር ኦር ዳንኤሊ እና የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤናው ዘርፍ አብሮ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
ኢትዮጵያ እና እስራኤል በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ክትባት በጋራ ለማምረት በሚቻልበት ሁኔታ፣ የአቅም ግንባታ፣ የጤና ዘርፍ ኢንቨስትመንት እና በሁለቱ ሀገራት ጤና ሚኒስቴር መካከል ትብብር ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ማድረጋቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ