ሀገራት ሽብርተኝነትን በጋራ ለመፋለም እየመከሩ ነው፡፡

152
ሀገራት ሽብርተኝነትን በጋራ ለመፋለም እየመከሩ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 23/2013 ዓ.ም (አሚኮ)በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጽሕፈት ቤት ሽብርተኝነትን በጋራ መከላከል ላይ ያተኮረ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በሰላም ሚኒስቴር የሕግ ማስከበር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ፍሬዓለም ሽባባው በውይይቱ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ሚኒስትር ዴዔታዋ በድርጅቱ የ72 ዓመታት የቋሚ አባልነት ታሪክ ያላት ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት እያከናወነች ያለውን ተግባር ለጉባዔው አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ትልቅ አጋርነት ያላት ሀገር መሆኗንም ገልጸዋል።
አሁን በደረስንበት የቴክኖሎጂ ዘመን ሀገራት ከሽብርተኝነት ጋር የተያያዙ አዳዲስ ፈተናዎችን በምን መልኩ ሊፋለሙ ይገባል በሚል ሐሳብ ዙሪያ 200 የዓለም ሀገራት እና የፀረ ሽብር ሥራን የሚያከናወኑ ተቋማት ተሳታፊዎች ናቸው።
ሽብረተኝነትን ለመከላከል ሀገራት በጋራ አብረው መቆም እንደሚገባቸው መገለጹን ከሰላም ሚኒስቴር የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article618 የምርጫ ውጤት ወደ ማዕከል መድረሱን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
Next article“በኢትዮጵያ የታሪክ ሰንሰለት ውስጥ ትንናንት፣ ዛሬን እና ነገን የሚያገናኙት የጎንደር ዓለም አቀፋዊ ቅርሶች የሕልውና አደጋ ውስጥ ናቸው” አቶ ጌታሁን ስዩም