
በሰሜን ሸዋ ዞንና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በተፈጠረው ችግር ከቀያቸው ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 22/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በተፈጠረው ችግር ከቀያቸው ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ጃንጥራር አባይ በአጣዬ ከተማ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠልለው ከሚገኙ ተፈናቃዮች ጋርም ውይይት አድርገዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ ወደ ዕለት ተለት መደበኛ እንቅስቃሴያቸው መመለስ እንዲችሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡ ኢብኮ እንደዘገበው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ