
የትራንስፖርት ሚኒስቴር ክረምቱን በሚካሄደው የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት ላይ በአጋርነት እየተሳተፈ መሆኑን ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 22/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ዛሬ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተካሄደ የአንዲት አቅመ ደካማ ቤት እድሳት ላይ ተሳትፈዋል።
ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አንዱ አካል በሆነው የቤት እድሳት ላይ በአጋርነት እየተሳተፈ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ሚኒስቴሩ በተያዘው ክረምት በወረዳው ለማደስ ከታቀዱ የአቅመ ደካሞች ቤቶች መካከል ሰላሳ በሚሆኑት ላይ እገዛ ያደርጋል ብለዋል።
ከዚህም ባለፈ አልግሎት የማይሰጡ 4 የኮንቴይነር ቤቶች በትራንስፖርት ሚኒስቴር አማካኝነት እድሳት ተደርጎላቸው ለአቅመ ደካሞች መተላለፋቸውን ገልጸዋል።
በክፍለ ከተማው በዚህ ክረምት 200 ቤቶችን ለማደስ የታቀደ ሲሆን ይህ ተግባር ክረምቱን ተከትሎ ለችግር የሚዳረጉ በርካቶችን ለመታደግ ያግዛልም ተብሏል። ኢብኮ እንደዘገበው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ