
ከፈረንሳይና ከጣሊያን መንግሥታት ጋር የተደረጉ የመከላከያ ስምምነቶች ጸደቁ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 22/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 6ኛ ዓመት 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ከፈረንሳይ መንግሥትና ከጣሊያን መንግሥት ጋር የተደረገውን የመከላከያ ትብብር ስምምነት አስመልክቶ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ።
የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጌታቸው ኃይለማርያም እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ ወይዘሮ ብርቱካን አያኖ ስለስምምነቶቹ ጠቀሜታ አስረድተዋል።
በተጨማሪ ፓርላማው የፌዴራል ዋና ኦዲተር ያቀረበውን የተለያዩ ተቋማትን የ2012 በጀት ዓመት የሒሳብ ኦዲት ግኝት ሪፖርት እያዳመጠ እንደሚገኝ ኢፕድ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ