‹በዕውቀትና በክዕሎት የበለጸገ ዜጋ ማፍራት ካልተቻለ የሀገርን ልማት እና ስልጣኔ ማረጋገጥ አይቻልም›› የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ንጉስ ታደሰ

147
‹በዕውቀትና በክዕሎት የበለጸገ ዜጋ ማፍራት ካልተቻለ የሀገርን ልማት እና ስልጣኔ ማረጋገጥ አይቻልም›› የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ንጉስ ታደሰ
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 22/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ1999 ዓ.ም ከተቋቋሙት የሁለተኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት የሠራተኛውን ቁጥር፣ የተማሪዎችን ቅበላ አቅም እና የሚሰጠውን የቅድመ እና የድህረ ስልጠና ዘርፍ እያሳደገ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ንጉስ ታደሰ ገልጸዋል፡፡
ዶክተር ንጉስ እንዳሉት ያለንበት ዘመን ዓለም አቀፍ ዕውቀት እና ምርምር የሚጠይቅ የቴክኖሎጅ ዘመን በመሆኑ ኢትዮጵያም ለትምህርት ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ትገኛለች፡፡ በዕውቀት፣ በክህሎትና በአስተሳሰብ የበለጸገ ዜጋ ማፍራት ካልተቻ የሀገርን ልማት እና ስልጣኔ ማረጋገጥ እንደማይቻልም አንስተዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ጥራት ያለው ትምህርት እና ስልጠና፣ ጥናት እና ምርምሮችን እንዲሁም የማማከር እና የማኅበረሰብ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ዶክተር ንጉስ ገልጸዋል፡፡
ከዚህም ባለፈ ለዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ ስለ ታላቁ ህዳሴ ግድብ እንዲገነዘብ በማድረግ እና 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዩኒቨርሲቲው መድረኮችን አዘጋጅቷል ብለዋል፡፡
በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ለተጎዱ ዜጎች ማቋቋሚያ የሚውል ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉንም ጠቅሰዋል፡፡
እጩ ተመራቂዎችም በዩኒቨርሲቲው የቀሰሙትን ትምህርት እና ወደ ማኅበረሰቡ ሲቀላቀሉ የሚያገኙትን ልምድ በማዋሐድ ያስተማራቸውን ኅብረተሰብ በቅንነት እንዲያገለግሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊት 26 ሺህ 350 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡ ዛሬ ደግሞ 3 ሺህ 115 ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው፡፡ ከእነዚህ ውስጥም 39 ሁለተኛ ዲግሪ 2 በሶስተኛ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡
በዳግማዊ ተሰራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article28 ታዳጊ ኢትዮጵያውያን ከታንዛኒያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
Next articleከ1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ገለጸ፡፡