
28 ታዳጊ ኢትዮጵያውያን ከታንዛኒያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 22/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በህገወጥ ስደት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሚደረግ ጉዞ ከሀገር ወጥተው የታንዛኒያን ድንበር ጥሰው ሲገቡ በሀገሪቱ ፖሊስ ተይዘው የነበሩ 28 ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ታዳጊዎቹ ከሌሎች ከ18 ዓመት በላይ ከሆኑ 36 ስደተኞች ጋር ተይዘው የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ይህን ተከትሎ የታንዛኒያ መንግሥት እድሜያቸው አነስተኛ የሆኑትን ለማሰር የማይችል በመሆኑ በአፋጣኝ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ኤምባሲው ሁኔታውን እንዲያመቻች ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የተመለሱ መሆኑን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያወጣው መረጃ ያመላክታል።
በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች በታንዛኒያ እስር ቤቶች በእስራት ላይ የሚገኙ በመሆኑ ኹሉንም ዜጎች ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ኤምባሲው አመላክቷል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ