
ባሕር ዳር፡ መስከረም 10/2012 ዓ.ም (አብመድ) አሜሪካ ባለፈው ሐሙስ በአፍጋኒስታን በሰው አልባ አውሮፕላን በፈጸመችው ጥቃት 30 አርሶ አደሮች መገደላቸውን አመነች፡፡ አሜሪካ እንዳለችው ጥቃቱ ዒላማ ያደረገው አይ ኤስ አይ ኤል የተደበቀባቸውን አካባቢዎች ነበር፤ ነገር ግን በአካባቢው የነበሩ 30 ለውዝ አምራች አርሶ አደሮች ተገድለዋል፤ ቢያንስ 40 የሚደርሱ ደግሞ ቆስለዋል፡፡
ጥቃቱ የደረሰበት አካባቢ በአሜሪካ የሚደገፉ ኃይሎች የሚቆጣጠሩት መሆኑ ደግሞ በዘገባው ተመላክቷል፡፡
‹‹መጀመሪያ ላይ በአካባቢው የአይ ኤስ አይ ኤል አባላት መደበቃቸውን የሚያመላክት መረጃ ነበረን፤ ለዚያ ነው ጥቃቱን የፈጸምነው›› ብለዋል አንድ በአፍጋኒስታን የሚገኘው የአሜሪካ ጦር ቃል አቀባይ ለአልጀዚራ በሰጡት መረጃ፡፡
የአፍጋኒስታን መንግሥት ሁኔታውን እያጣራ እንደሚገኝም ተሰምቷል፡፡ በጥቃቱ ከሞቱት ውስጥ እስካሁን የዘጠኝ ሰዎችን አስከሬን ብቻ ማግኘት መቻሉም ተዘግቧል፡፡
ምንጭ፡- አልጀዚራ