የሀገር መከላከያ ሠራዊት በብር ሸለቆ ያሰለጠናቸውን መሠረታዊ ወታደሮች እያስመረቀ ነው።

606
የሀገር መከላከያ ሠራዊት በብር ሸለቆ ያሰለጠናቸውን መሠረታዊ ወታደሮች እያስመረቀ ነው።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 22/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት በብርሸለቆ መሠረታዊ ወትድርና ማሰልጠኛ ትምሕርት ቤት ያሰለጠናቸውን ወታደሮች እያስመረቀ ነው። የሀገር ኩራት፣ የወገን ጠበቃ፣ የራስን ሕይወት ትተው ለውድ ሀገራቸው ፅኑ ቃል ኪዳን ያሰሩት የኢትዮጵያ ልጆች በብር ሸለቆ አደራ እየተቀበሉ ነው። አደራው ከዘመን ዘመን የማይታጠፍ የማይሻር፣ የማይሸነፍ የእምዬ ኢትዮጵያ ነው። የእናት አደራቸውን ተቀብለው ኢትዮጵያን ሊያስከብሩ፣ ኢትዮጵያውያንን ሊያኮሩ፣ ጠላትን ሊያስደነብሩ ስልጠናቸውን አጠናቅቀው እነሆ ብር ሸለቆ ላይ አደራቸውን ተቀብለው ቃላቸውን እያሰሩ ነው።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የመከላከያ ሚኒስቴር የሰው ሀብት ልማት ዘርፍ ዋና ኃላፊ ሜጄር ጄኔራል ሐጫሉ ሸለመ፣ የምድር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ምክትል አዛዥ ለሰው ሀብት ልማት ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳንን ጨምሮ ከፍተኛ ጄኔራል መኮንኖች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ – ከብርሸለቆ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“የፌዴራል መንግሥት የመተከል ዞን ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ይዟል” የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ቴክኒክ ኮሚቴ
Next articleደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለ13ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከ3 ሽህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው፡፡