እስካሁን 378 ምርጫ ክልሎች ውጤታቸውን ቦርዱ ላቋቋመው የውጤት አጣሪ ቡድን ማስረከባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ።

161

እስካሁን 378 ምርጫ ክልሎች ውጤታቸውን ቦርዱ ላቋቋመው የውጤት አጣሪ ቡድን ማስረከባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ።

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 21/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስካሁን 378 ምርጫ ክልሎች ውጤታቸውን ቦርዱ ላቋቋመው የውጤት አጣሪ ቡድን ማስረከባቸውን ገልጿል፡፡

ምርጫ ክልሎች በክልላቸው ውጤታቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ወደ ውጤት አጣሪ ቡድኑ ይዘው በመምጣት በምርጫ ቀሳቁስ ወቅት ከተሰራጩ ቁሳቁስና አሁን በውጤቱ ይፋ መደረግ ያለውን እውነት በማመሳከር ቡድኑ ውጤቱን ይፋ ያደርጋል ብለዋል የምርጫ ኦፕሬሽን ኃላፊዋ ሃና አበበ።

የምርጫ ክልሎች ውጤታቸውን በሕዝብና በፓርቲ ታዛቢዎች በኩል አሽገው ነው ወደ ማእከል የሚልኩት።

ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ – ከአዲስ አበባ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል፡፡
Next articleፖለቲካ ፓርቲዎች በድህረ-ምርጫ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሕዝብን አንድነት የሚያጠናክር እንዲሆን ተጠየቀ፡፡