ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተናን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

658

ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተናን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 21/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 እስከ 25/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገልጿል። በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የፈተናው ወረቀት መድረሱን በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ባለሙያና ተወካይ ቡድን መሪ ኀይሉ ታምር ጠቁመዋል።

ፈተናው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ በየደረጃው ያሉ የጸጥታ አካላት እየሠሩ እንደሚገኝ ተወካይ ቡድን መሪው ተናግረዋል።

አቶ ኀይሉ እንዳሉት ተማሪዎች ለፈተናው ዝግጁ እንዲኾኑ መሸፈን የሚገባቸው የትምህርት ይዘቶች እንዲሸፈኑ ሰፊ ሥራ ሲሠራ ቆይቷል። ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው ለተቋቋመው ግብረ ኀይል በቂ የሥራ መመሪያ እየተሰጠ ነው ብለዋል። ሁሉም ኀላፊነት የተሰጣቸው አካላት ኀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡም ጠይቀዋል።

ነገ ለኹሉም ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተናው አሰጣጥ መመሪያ ስለሚሰጥ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ተገኝተው እንዲከታተሉ አቶ ኀይሉ አሳስበዋል።

ከሰኔ 23 እስከ 25/2013 ዓ.ም በሚሰጠው ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና 412 ሺህ 497 ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ፡፡ 5 ሺህ 521 ትምህር ቤቶች ደግሞ ፈተናውን እንደሚሰጡ ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleከስድስተኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ ማግስት ከፖለቲካ ፓርቲ ኀላፊዎች ጋር ተገናኝተው መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ተናገሩ፡፡
Next articleባህላዊ ህክምና በጤና ዘርፉ ውስጥ ሕጋዊ ሥርዓት ይዞ አገልግሎት እንዲሰጥ እየተሠራ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።