የአፍሪካውያን በጋራ መሥራት ለአህጉሩ ቀጣይ ልማትና እድገት ወሳኝ መሆኑን የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ገለጹ።

155
የአፍሪካውያን በጋራ መሥራት ለአህጉሩ ቀጣይ ልማትና እድገት ወሳኝ መሆኑን የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ገለጹ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 21/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ደቡብ ሱዳን የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በጋራ ለመሥራት ተግባራዊ በመሆን ላይ የሚገኘውን የላፕሴት ፕሮጀክት አፈጻጸምን በሚዳስሰው ጉባዔ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
በጉባዔው የሦስቱ ሀገራት የትራንስፖርት ሚኒስትሮች እና ባለሙያዎች፣ የአፍሪካ ሕብረት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም አምባሳደሮች ተገኝተዋል።
በጉባኤው የሚስተዋሉ ችግሮችን በመገምገም የጋራ መፍትሔ ለማምጣት ዓላማ ያደረገ ነው፤ በመድረኩ ወይዘሮ ዳግማዊት የአፍሪካውያን በጋራ መሥራት ለአህጉሩ ቀጣይ ልማትና እድገት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የላፕሴት ፕሮጀክት በ5 ቢሊየን ዶላር በሦስቱ ሀገራት የወደብ፣ የባቡር መስመር ዝርጋታ፣ የነዳጅ መስመር ዝርጋታ፣ የመንገድና የቱሪዝም ልማትን በመተግበር ሦስቱን ሀገራት በኢኮኖሚ የሚያስተሳስርና በጋራ መልማትን ዓላማ ያደረገ ፕሮጀክት ነው ተብሏል።
የላፕሴት ፕሮጀክት በሥሩ በርካታ የልማት ፕሮጀክቶችን ይዟል፤ ከዚህ ውስጥ በ480 ሚሊየን ዶላር በመገንባት ላይ የሚገኘው የላሙ ወደብ አንዱ ነው። የላሙ ወደብ ፕሮጀክት በሦስት ደረጃ እየተገነባ መሆኑ ተገልጿል፤ የመጀመሪያውን ደረጃ ማጠናቀቅ መቻሉም ተነስቷል። ይህ ወደብ ሦስቱን ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርግ እና ፈጣን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በቀጣናው ብሎም በአህጉሩ እንደሚፈጥር ታምኖበታል፤ ኢትዮጵያም በወደቡ 20 ሄክታር መሬትን አግኝታለች፤ በኢንዱስትሪ እና ማኑፋክቸሪንግ ማልማት እንደምትችል ታውቋል።
በጉባኤው በላፕሴት ፕሮጀክቶች እና በላሙ ወደብ አፈጻጸም ዙሪያ ሦስቱ ሀገራት በሚኒስትሮች ደረጃ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፤ በተስተዋሉ ችግሮች በመገምገም የጋራ መፍትሔ ለማምጣት ዓላማ አድርጓል።
የፕሮጀክቶቹን ቀጣይ ሥራዎችን ለማስፈጸም የሚያስችል የፊርማ ሥነ ሥርዓትም በሦስቱ ሀገራት ዛሬ ይከናወናል። ፋብኮ እንደዘገበው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበጅግጅጋ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የእርዳታ ስንዴ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
Next articleከስድስተኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ ማግስት ከፖለቲካ ፓርቲ ኀላፊዎች ጋር ተገናኝተው መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ተናገሩ፡፡