በጅግጅጋ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የእርዳታ ስንዴ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

234
በጅግጅጋ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የእርዳታ ስንዴ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 21/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ከሰኔ 12 እስከ ሰኔ 18/2013 ዓ.ም ድረስ ከ56 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል፡፡
ከነዚህ የኮንትሮባንድ እቃዎች አንዱ 33 ሚሊየን 100 ሺህ ብር ግምት ያለው ለዕርዳታ እንዲውል ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆኖ ወደ ሀገር ገብቶ በጅግጅጋ ሲንቀሳቀስ የተያዘ ስንዴ ነው፡፡
በሳምንቱ ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች
• የገቢ ኮንትሮባንድ 54 ሚሊዮን 211 ሺህ 562 ብር
• ወጪ ደግሞ 2 ሚሊዮን 722 ሺህ 916 ብር ግምት አላቸው፡፡
ከእቃዎቹ መካከል ስንዴ፣ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ መድኃኒትና ሌሎች ናቸው፡፡ 32 ያህል ተሽከርካሪዎች ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ ተይዘዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ለኮንትሮባድ እቃዎቹ መያዝ ኅብረተሰቡ ብሎም የጸጥታ አካላት ላደረጉት ትብብር ምስጋናውን ገልጿል፡፡ በቀጣይም ኮንትሮባድ ለመከላከል በሚያከናወነው ሥራ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሚኒስቴሩ ጠይቋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ማሻሻያዋ እያደረገች ያለችዉ አንዱ ለዉጥ የሀገር በቀል ምርቶችን በግብዓትነት መጠቀም እንደኾነ ተገለጸ፡፡
Next articleየአፍሪካውያን በጋራ መሥራት ለአህጉሩ ቀጣይ ልማትና እድገት ወሳኝ መሆኑን የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ገለጹ።