
በመዲናዋ የሚገነበው የአማራ ባህል ማዕከል አልማ ለሚያከናውነው የልማት ስራ አጋዥ እንደሚሆን ተገለጸ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 20/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ባህል ማዕከል ግንባታ የአማራ ሕዝብ ባህልና ትውፊት ተጠብቆ እንዲቆይ
ከማድረግ ባሻገር የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) የሚያከናውናቸውን የልማት ስራዎች እንደሚያግዝ ተገልጿል።
በአዲስ አበባ የአማራ ባህል ማዕከል መገንቢያ ቦታ ርክክብን በማስመልከት የምስጋና መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
የባህል ማዕከሉ አልማ የሚያደርጋቸውን ዘርፈ ብዙ የልማት እንቅስቃሴዎች የሚደግፍ መሆኑን የልማት ማኅበሩ ዋና ሥራ
አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፋንታ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ
በበኩላቸው አልማን መደገፍ በአማራ ክልል በድህነት ምክንያት ችግር ውስጥ የወደቁ ዜጎችን መደገፍ ነው ብለዋል።
በመድረኩ የተሳተፉት በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸው የአማራ ሕዝብ ከሌሎች
ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹ ጋር ሆኖ ሀገሪቱን ለመገንባት በሚያደርገው እንቅስቃሴ የባህል ማዕከሉ ግንባታ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ
ለግንባታው ሁሉም ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። ኢብኮ እንደዘገበው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m