በትውልድ ጀርመናዊ የኾኑ የፍራንክፈርት ሆቴል ባለቤት 10ሺህ ዩሮ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቦንድ ለመግዛት ቃል መግባታቸው ተገለጸ።

121
በትውልድ ጀርመናዊ የኾኑ የፍራንክፈርት ሆቴል ባለቤት 10ሺህ ዩሮ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቦንድ ለመግዛት ቃል መግባታቸው ተገለጸ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 20/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ)በጀርመን ፍራንክፈርት ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የቦንድ ግዥ ፈጽመዋል፡፡
በጀርመን፣ ፍራንክፈርት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች እና ምሁራን የተሣተፋበት በኢፌዴሪ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የ16 ሺህ ዩሮ ቦንድ ግዥ ተፈጽሟል። ኢትዮጵያውያኑ የ67 ሺህ ዩሮ ቦንድ ግዢ ለመፈጸምም ቃል መግባታቸው ተገልጿል፡፡
በዕለቱ በጀርመን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አራት የካርጎ ኤጀንቶች የ12 ሺህ ዩሮ ቦንድ ግዢ የፈጸሙ ሲሆን በቀጣይም የ55 ሺህ ዩሮ ቦንድ ለመግዛት ቃል ገብተዋል።
በትውልድ ጀርመናዊ የኾኑ የፍራንክፈርት ሆቴል ባለቤት 10ሺህ ዩሮ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቦንድ ለመግዛት ቃል ገብተዋል።
በገቢ ማሰባሰቢ መርሃግብሩ የታደሙት ሀገር ወዳዶቹ የዲያስፖራ አባላት ከቦንድ በተጨማሪ በሰሜን ሸዋ አካባቢ በጸጥታ ችግር ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም 14 ሺህ 500 ዩሮ ድጋፍ አድርገዋል ።
በፍራንክፈርት የኢፌዴሪ ቆንስል ጄኔራል ፈቃዱ በየነ በመርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሀገርን ጥሪ ተቀብለው የሚወዷትን ሀገራቸው ለመደገፍ በመገኘታቸው ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡
በጀርመን ፍራንክፈርት አከባቢ የሚኖሩ ባለሀብቶች በሁሉም ዘርፍ ሀገራቸውን ሲደግፉ የነበሩ በአንድም በሌላ መንገድ አሻራቸውን ሲያሳርፉ የኖሩ የሀገር ባለውለታዎች መሆናቸውን አቶ ፈቃዱ ተናግረዋል፡፡
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቦንድ ግዥ እና በጸጥታ ምክንያት በሰሜን ሸዋ አከባቢ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የተለመደ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉና በሁሉም ዘርፍ በቀጣይነት ከሀገራቸው ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፏል።
በጀርመን ፍራንክፈርት አከባቢ የሚኖሩ ሀገር ወዳዶቹ ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የሁሉም በመኾኗ ድጋፋቸውን ለሚሹ ወገኖች ለመድረስ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ወደ ኋላ እንደማይሉ መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በማኀበራዊ ትስስር ገጹ አስነብቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየሽብርተኛው የህወሃት ቡድን ርዝራዦችን አድኖ በመያዝ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የተጀመረው ዘመቻ ተጠናክሮ ይቀጥላል” ኮሚሽኑ
Next articleʺእኔስ በተከዜ ቀናሁ፤ እርሱን ብሆን ብዬ ተመኘሁ”