
ከሳዑዲ አረቢያ 380 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 19/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሳዑዲ አረቢያ ያለ መኖሪያ ፈቃድ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተው ማረሚያ ቤት ከነበሩ ኢትዮጵያውያን መካከል 380 ዎቹ ወደ አገራቸው ተመለሱ።
ዛሬ በሚደረጉ አምስት ተመሳሳይ በረራዎች ሁለት ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ይጠበቃል፡፡
ከስደት ለተመለሱት ወገኖች አቀባበል ያደረጉላቸው የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬአለም ሽባባው፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ናቸው፡፡ ኢዜአ እንደዘገበው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m