ከሳዑዲ አረቢያ ዜጎችን ወደ ሀገር መመለስ እንደሚጀመር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

135

ከሳዑዲ አረቢያ ዜጎችን ወደ ሀገር መመለስ እንደሚጀመር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 19/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) ቀይ ባህርን በማቋረጥ ሕጋዊ ባልኾነ መንገድ የሳዑዲ አረቢያን ድንበር ጥሰው ሲገቡ በሳዑዲ የሕግ አስከባሪ አካላት ተይዘው እና የሳዑዲ የመኖርያና የሥራ ፈቃድ ሕግጋትን ተላልፈው በመገኘታቸው በስደተኞች ማቆያ ጣብያዎች ከአንድ ዓመት በላይ በእስር የቆዩ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ሚኒስትሩ ገልጿል።

እነዚህ እስረኞች በተለይ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ ረዘም ላለ ግዜ በእስር በመቆየታቸው ሳብያ በቤተሰቦቻቸውና በማኅበረሰቡ ላይ ከፍተኛ የሥነ-ልቡና ጫና አሳድሮ ቆይቷል፡፡ በቅርቡ መንግሥት እነዚህ እስረኞች በሙሉ ወደ ሀገር እንዲገቡ ያስቀመጠውን አቅጣጫ ተከትሎ ብዛት ያላቸው በረራዎች እንዲኖሩ ከሳዑዲ ጋር በመነጋገር መሳካቱን ነው ሚኒስትሩ የገለጸው።

ይህን ለማሳካት የሁለቱ ሀገራት መንግሥታት ባደረጉት ስምምነት መሰረት ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቋሞ ዜጎች በስፋት ወደ ሀገር የመመለስ ሂደትን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ወገን ቀዳሚ ልዑክ ተልኮ ከሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ ዜጎችን የማስመለስ ስራ እንዲሠራ መግባት ላይ እንደተደረሰ ጠቁሟል።

በዚሁ መሰረት ከሰኔ 19/2013 ዓ.ም ጀምሮ በየቀኑ እስከ ስድስት በሚደርሱ የሳዑዲና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች በማቆያ ጣብያዎች የነበሩ ዜጎች የሚያመላልሱ እንደኾነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በማሕበራዊ ትስስር ገጹ አብራርቷል።

በዛሬው ዕለትም ቁጠራቸው ከ2 ሺህ በላይ የኾኑ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱም ታውቋል፡፡ ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ቃልአቀባይ ጽሕፈት ቤት ነው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ የአፍሪካ የአመራር ልህቀት ማዕከል በሚል ስያሜውን በይፋ ዛሬ ይቀይራል።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን መርቀው ከፈቱ፡፡