
የመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ የአፍሪካ የአመራር ልህቀት ማዕከል በሚል ስያሜውን በይፋ ዛሬ ይቀይራል።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 19/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞ የመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ ይባል የነበረውን ተቋም ስያሜ የአፍሪካ የአመራር ልህቀት ማዕከል በሚል እንዲሰየም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰኔ 15/2013 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡
የአካዳሚው የስም ለውጥ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የአመራር ጥያቄዎችን ማሟላት የሚያስችል አቅም ያላቸውን ልሂቃን የሚያፈራ መሆኑን ይገልጻል ተብሏል፡፡
የዕድገት ተኮር አስተሳሰብን የሚያንፀባርቅ የትምህርት ተቋም ማድረግን በሚመጥን እና በሚገልጽ መልኩ በአዲስ እንደተደራጀም ተገልጿል፡፡
ዛሬ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት በስሉሉታ ከተማ ያስገነባው አዲስ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በይፋ ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡- ጋሻው ፋንታሁን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m