
በትግራይ ክልል የአሸባሪው ሕወሓት ርዝራዥ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ የሰብዓዊ ድጋፍ በሚያደርጉ ሁለት ኢትዮጵያን እና አንድ ስፔናዊት ላይ ጥቃት ተፈጸመ።
ባሕር ዳር: ሰኔ 18/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለፀው አቢ አዲ በተባለ ስፍራ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ሠራተኛ በሆኑ ሰዎች ላይ በአሸባሪዉ ኃይል ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። በዚህም መንግሥት የተሰማዉን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል።
መንግሥት በተደጋጋሚ ለጋሽ እና እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች የጸጥታ እና የስጋት አካባቢዎች ላይ ለሠራተኞች ደኅንነት ሲባል ማንኛውም እንቅስቃሴ በመከላከያና በጸጥታ አካላት ታጅበዉ ለዜጎች እንዲያደርሱ ሲመክር መቆየቱ ይታወሳል።
ይሁን እንጅ አልፎ አልፎ የተወሰኑ ሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶቾ ከመንግሥት እውቅና ዉጭ ሲንቀሳቀሱ ይስተዋላል፤ ይህም የከፋ ችግር እያስከተለ ነው።
ውሉ ባልታወቀ ዓላማ የንጹሐን ሞት ዛሬም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኝት የሚሯሯጠዉ የአሸባሪዉ ሕወሓት የተበታተኑ ሽፍታዎችን ለሕግ ለማቅረብ መንግሥት ዛሬም ሕዝባዊነቱን ጠብቆ ለዜጎች ሰላም እና ለሀገሪቱ ሉዓላዊነት ይሠራል ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m