ደቡብ ሱዳን የናይል ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት ማቀዷን ገለጸች።

98

ደቡብ ሱዳን የናይል ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት ማቀዷን ገለጸች።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 18/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) ደቡብ ሱዳን የናይል ወንዝን በመጠቀም የኀይል ማመንጫ ግድብ ለመገንባት ዕቅድ
ማዘጋጀቷን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴንግ ዳው ዴንግ ማሌክ ለናሽናል ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ከዕርስ በርስ ጦርንት የተላቀቀችው
ደቡብ ሱዳን ወደ ኢንዱስትሪ መር የገበያ ስርዓት ለመሸጋገር የሚያስችል ኀይል ማመንጫ ግድብ ለመገንባት የሚስችል ገንዘብ
አላት።
የግድብ ግንባታ ፕሮጀክቱ መንግሥት ከነዳጅ ሽያጭ በሚያገኘው ገቢ ለመገንባት ዕቅድ ከተያዙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ
መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን ርካሽ፣ ታዳሽ እና በሀገሪቱ በየጊዜው የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ መከላከል የሚያስችል የግዙፍ ግድብ ግንባታን
በይፋ ለማስጀመር ዕቅድ መያዟን ተናግረዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን በየወቅቱ በሚፈጠር የጎርፍ አደጋ፣ በኀይል እጥረት፣ የውኃ እጥረት እና በደካማ የመሰረተ-ልማት ችግር
እንደምትሰቃይ ጠቅሰዋል።
ወደ ኢንዱስትሪ መሸጋገር የሚቻለው በቅድሚያ የኀይል አቅርቦት አስተማማኝ በሆነ መልኩ ማምረት ሲቻል እንደሆነ እና ግድቡ
የኀይል ፍላጎትን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
ግድቡ ምን ያህል ርዝመት፣ ምን ያህል ውኃ መያዝ እና ምን ያህል ኀይል የሚያመነጩ ተርባይኖች ሊኖሩት እንደሚገባ የሚሳይ
መነሻ ዝርዝር ዕቅድ እና ጥናት በሀገሪቱ የመስኖ ሚኒስቴር በኩል መከናወኑ በዘገባው ተመላክቷል፡፡
ደቡብ ሱዳን ይህን ግድብ የመገንባት ሉዓላዊ መብት እንዳላት ምክትል ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እየገነባች ባለችው ግዙፍ ግድብ ምክንያት የሚነሱ አለመግባባቶች በትብብር መንፈስና በውይይት መፈታት
እንዳለባቸው ምክትል ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
“የአባይ ወንዝ ከፈጣሪ ለአካባቢው ሲሰጥ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንድንጠቀምበት እንጂ የግጭት መክንያት እንዲሆን
አይደልም” የሚሉት ምክትል ሚኒስትሩ ደቡብ ሱዳን በሶስቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረው ውዝግብ በውይይትና በድርድር ብቻ
መፈታት እንደሚገባው እንደምታምን ገልጸዋል፡፡
እንደዚህ ያለ ግዙፍ ፕሮጀክት ለመገንባት በቀዳሚነት የሚስፈልገው የገንዘብ አቅም መኖር እንደሆነ ያመላከቱት ማሌክ ደቡብ
ሱዳን አሁን ላይ ይህን የማድረግ አቅም አላት ብለዋል፡፡ ዘገባው የኢዜአ ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleኢትዮጵያ የድንቅነሽ ቅጂ በዩኔስኮ ጽሕፈት ቤት በቋሚነት ለዕይታ እንዲቀርብ አበረከተች።
Next articleበትግራይ ክልል የአሸባሪው ሕወሓት ርዝራዥ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ የሰብዓዊ ድጋፍ በሚያደርጉ ሁለት ኢትዮጵያን እና አንድ ስፔናዊት ላይ ጥቃት ተፈጸመ።