ኢትዮጵያ የድንቅነሽ ቅጂ በዩኔስኮ ጽሕፈት ቤት በቋሚነት ለዕይታ እንዲቀርብ አበረከተች።

95

ኢትዮጵያ የድንቅነሽ ቅጂ በዩኔስኮ ጽሕፈት ቤት በቋሚነት ለዕይታ እንዲቀርብ አበረከተች።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 18/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ የድንቅነሽ (ሉሲ) ቅጂ በዩኔስኮ ጽሕፈት ቤት በቋሚነት ለዕይታ እንዲቀርብ
ማበርከቷን በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ አስታውቀዋል፡፡
በድርጅቱ ጽሕፈት ቤት የምትቀርብበት ሥነ-ስርዓትም ተካሂዷል፡፡
አምባሳደር ሄኖክ ኢትዮጵያ የድንቅነሽን ቅጂ ለዩኔስኮ በማበርከቷ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ድንቅነሽ ዘር፣ ጎሳና ሃይማኖት
ሳንለይ የጋራ ሰብዓዊነታችን መገለጫ ናት ብለዋል፡፡
በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የተቀረፀ ንግግርም በሥነ ስርዓቱ ላይ ቀርቧል፡፡ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ኢትዮጵያ
ምድረ ቀደምት እንደሆነች ተንጸባርቋል።
በመርሃ ግብሩ የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ኦድሬ አዙሌ፣ የሉሲን ቅሪተ አካል ያገኘው ቡድን አባላት ፕሮፌሰር ዶናልድ ጆሃንሰን እና
ኢቭ ኮፐንስ እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች መገኘታቸውን የአምባሳደር ሄኖክ ተፈራን ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ጠቅሶ
ኢብኮ ዘግቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር እና በእገታ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
Next articleደቡብ ሱዳን የናይል ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት ማቀዷን ገለጸች።