“የመተከል ተፈናቃዮች በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸውና ምንም አይነት የጸጥታ ስጋት እንዳይገጥማቸው እየተሠራ ነው” የተፈናቃዮች አስመላሽ ግብረ ኀይል

155
“የመተከል ተፈናቃዮች በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸውና ምንም አይነት የጸጥታ ስጋት እንዳይገጥማቸው እየተሠራ ነው” የተፈናቃዮች አስመላሽ ግብረ ኀይል
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 18/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) ከመተከል ዞን ተፈናቅለው የቆዩ ዜጎችን ወደ ቀያቸው በመመለስ የማቋቋም ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡ ተፈናቃዮቹ ወደ ማንዱራ፣ ድባጤ፣ ቡለንና ዳንጉር ወረዳዎች በመመለስ በአንድ ማዕከል ለጊዜው እንዲቆዩ እንደሚደረግ የተፈናቃዮች አስመላሽ የቴክኒክ ግብረኀይል አባል በትግሉ ተስፋዬ አስረድተዋል፡፡
ተፈናቃዮቹን በማስመለሱ ሂደት ውስጥ ከመተከል ዞን የተፈናቀሉ ዜጎችን ብቻ ሳይኾን ከግልገል በለስ የተፈናቀሉ ዜጎችንም ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራ እንደሚከናወን አቶ በትግሉ ተናግረዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ ዘለቄታዊ የኾነ ሕይወት መኖር እስኪጀምሩ ድረስ በአንድ ማዕከል እንዲቆዩ ይደረጋል ያሉት አቶ በትግሉ ተፈናቃዮች በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚደረግላቸውና ምንም አይነት የጸጥታ ስጋት እንዳይገጥማቸው እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
ለተፈናቃዮቹ የጋራ የእርሻ መሬት ተዘጋጅቶላቸዋል፤ አስፈላጊውን ግብዓት ለማቅረብም እየተመቻቸላቸው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
አቶ በትግሉ ተፈናቃዮችን ወደነበሩበት አካባቢ ለመመለስ ከፌዴራል መንግሥት ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በቀጣይ ከማኅበረሰቡ ጋር የእርቀ ሰላም ጉባዔ እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ቡሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ሕብረት እየተደረገ ያለውን ድርድር ሱዳን እና ግብጽ እንዲያከብሩ የጸጥታው ምክር ቤትን ኢትዮጵያ ጠየቀች፡፡
Next articleየፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕወሓት የሽብር ቡድን አባላት ሕንጻዎች በገለልተኛ አስተዳዳሪ ተይዘዉ እንዲተዳደሩ ወሰነ።