
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና ሌሎች የዘርፍ ኮሚሽኖች የቀረበለትን ሹመት አጸደቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 18/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ምክር ቤቱ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና ሌሎች የዘርፍ ኮሚሽኖች የቀረቡለትን ሹመት አጸደቀ።
ምክር ቤቱ ወይዘሮ ራኬብ መሰለን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር አድርጎ ሹሟል።
ወይዘሮ መስከረም ገስጥን የሴቶችና ሕጻናት መብቶች ጉዳዮች ኮሚሽነር፣ ወይዘሪት እርግበ ገብረሃዋሪያን የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን መብቶች ጉዳዮች ኮሚሽነር አድርጎ ሹሟል።
ዶክተር አብዲ ጅብሪል ደግሞ የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ጉዳዮች ኮሚሽነር አድርጎ ሹሟል። ኢዜአ እንደዘገበው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ