በአጣዬ አካባቢ የተቋቋመው የኮማንድ ፖስት ያከናወናቸውን ሥራዎች እየገመገመ ነው።

115
በአጣዬ አካባቢ የተቋቋመው የኮማንድ ፖስት ያከናወናቸውን ሥራዎች እየገመገመ ነው።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 17/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአጣዬና አካባቢው ተፈጥሮ የነበረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ሥራ ከጀመረ አንስቶ ያከናወናቸውን ተግባራትና የተገኙ ለውጦችን በከሚሴ ከተማ በመገምገም ላይ ይገኛል።
የኮማንድ ፖስቱ ለማከናወን አቅዶ የነበራቸው፣ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር የማስቆምና ወደ መደበኛ ሁኔታ የመመለስ፣ ማኅበራዊና አስተዳደራዊ ሁኔታዎችን ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ፣ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተወሰዱ እርምጃዎችና ጥፋተኞችን ወደ ፍርድ ለማቅረብ የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ እንዲቀጥል ለማስቻል እና በአፈፃፀሙ ላይ የታዩ ክፍተቶችን ለመፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነው እየገመገመ የሚገኘው።
በግምገማው የዞንና የወረዳ የኮማንድ ፖስቱ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን፣ ለቀጣይ የሥራ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ምንጭ፡ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር ለመሥራት ስምምነት ተፈራረመ፡፡
Next article“ከቆመው ድልድይ ሥር የማይቆም ወንዝ አለና ፈፅሞ መቆም አይቻልም”