
“በአሸባሪው ሕወሓት ቡድን ላይ የተፈጸመዉን ጥቃት በንጹሐን ላይ እንደተፈጸመ አድርጎ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም” የኢፌዴሪ
መከላከያ ሠራዊት
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 17/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ
በሰጡት መግለጫ በትግራይ ክልል ከመቀሌ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘዉ “ቶጎጋ” በተባለ ቦታ የተፈፀመዉ የአየር ጥቃት
ሽብርተኛ ቡድኑን ዒላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
“በአሸባሪው ሕወሓት ቡድን ላይ የተፈጸመዉን ጥቃት በንጹሐን ላይ እንደተፈጸመ አድርጎ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም” ብለዋል፡፡
የአሸባሪው ሕወሓት ቡድን የጦር መሣሪያና ወታደሮችን ማርከናል ያሉትም ሐሰት ነው ብለዋል፡፡ “አሸባሪ ቡድኑ መንገዱ ሁሉ
ስለተዘጋበት ዓለምአቀፋዊ አጀንዳ በመፍጠር ከመንግሥት ጋር ለመደራደር የሚፈጥሩት በመሆኑ አይሳካላቸውም” ነው ያሉት፡፡
የትግራይ ሕዝብ ሰላምን ለማስጠበቅ ሠራዊቱ ሌት ከቀን በትጋት እያገለገለ እንደሆነ የገለጹት ኮሎኔል ጌትነት ሕዝቡም በውሸት
ፕሮፖጋንዳ የሚያደናግሩትን መለየት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ጽዮን አበበ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m