
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 3 ሺህ 572 አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 16/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ካሣሁን ተገኝ
አዲስ ተማሪዎችን ከሰኔ 24 እስከ ሰኔ25/2013 ዓ.ም ለመቀበል ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።
ተማሪዎችን በጎንደር የእንግዳ ተቀባይነት ባህል መሰረት ለማስተናገድ እየተሠራ ይገኛል ፤ ለዚህም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሠራ
መሆኑን ጠቁመዋል።
የተዋቀረው ኮሚቴ አዲስ ተማሪዎች እንግልት እንዳይገጥማቸው ከመናኸሪያ ጀምሮ እሰከ ዩኒቨርስቲው ግቢ ድረስ የትራንስፖርት
አገልግሎት በማዘጋጀት፣ የተማሪዎችን መኝታ ክፍል ቀድሞ በማዘጋጀት፣ የተማሪ መመገቢያ ማዕከላትን ምቹ በማድረግና
አስፈላጊ ግብዓቶችን በማሟላት ረገድ መሠራቱን ዶክተር ካሣሁን ያስታወቁት።
ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ከተቀበለ በኋላ ሰኔ 27/2013 ዓ.ም የመማር ማስተማር ቀንን ለመጀመር መታቀዱንም አመላክተዋል።
የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚሠራ ቡድን መቋቋሙንና በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልቶች ተማሪዎች ራሳቸውን ከወረርሽኙ
እንዲጠብቁ ለማስተማር ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከአዳዲስ ተማሪዎች ባሻገር ነባር የክረምት ተማሪዎችን ከሐምሌ 1 እስከ ሐምሌ 2/2013 ዓ.ም ለመቀበል
ተዘጋጅቷል።
ዘጋቢ፦ ፍፁምያለምብርሃን ገብሩ – ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m