በደቡብ ክልል ድምጽ የተሰጠባቸው 98 በመቶ የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ክልል ገብቷል፡፡

87
በደቡብ ክልል ድምጽ የተሰጠባቸው 98 በመቶ የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ክልል ገብቷል፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 16/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ክልል ደረጃ 98 በመቶ ድምጽ የተሰጠባቸው የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ክልል መግባት እንደቻለ የሲዳማ ክልልና የደቡብ ክልሎች ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
በደቡብ ክልል የተቀሩት የምርጫ ቁሳቁሶችም ወደ ምርጫ ክልል ከተወሰኑ ሰዓታት በኋላ የሚገባ መሆኑን የጽሕፈት ቤቱ ኀላፊ አቶ ፍሬው በቀለ ገልጸዋል፡፡
በሲዳማ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ እስከ ስድስት ሰዓት ድረስ ተጠቃሎ ወደ ምርጫ ክልል እንደሚገባ ኀላፊው ተናግረዋል፡፡
በሃዋሳ ከተማ በትናንትናው ዕለት ቆጠራው ተጠናቆ የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ክልል ተሰባስቦ መጠናቀቁንም ጠቁመዋል፡፡
በሲዳማ ደረጃ ትናንት የተካሄደው የድምፅ መስጠት ሂደት ስኬታማ ነበር ያሉት ኀላፊው የደቡብ ክልል የድምፅ መስጠት ሂደትም በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
ከተለያዩ የፖለቲካ ፖርቲዎች የቀረቡ ቅሬታዎችም በሚገባ የማጣራትና ውሳኔ የመስጠት ሥራ እንደሚከናወን መግለጻቸውን ፋብኮ ዘግቧል፡፡
በማጓጓዝ ሥራውም ምንም ችግር አለመግጠሙን ገልጸው መራጩን ሕዝብ ጨምሮ የጸጥታ ኃይሉ፣ የመገናኛ ብዙኃን፣ የምርጫ አስፈፃሚዎችና በምርጫው ሂደት ሚና የነበራቸውን አካላትን አመስግነዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleከ16ሺህ በላይ የመተከል ዞን ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የግብረ ኃይሉ ቴክኒክ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
Next article“በዓባይ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትክክለኛውን አቋምና ተጨባጭ እውነታ ማስረዳት ይገባዋል” በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር ዶክተር ጥጋብ በዜ