በሲዳማ ክልል የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ተጠናቀቀ።

122

በሲዳማ ክልል የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ተጠናቀቀ።

ባሕር ዳር: ሰኔ 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሲዳማ ክልል በድምጽ መስጫ ወረቀት እጥረት ምክንያት ምርጫው በተቋረጠባቸው ጣቢያዎች ምርጫው ዛሬም ቀጥሎ በማካሄድ ማጠናቀቅ መቻሉን በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማና ደቡብ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት በሲዳማ ክልል በቁሳቁስ እጥረት ምክንያት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን ለዛሬ ያስተላለፈው በክልሉ 19 የምርጫ ክልሎች ስር በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ነው።

በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማና ደቡብ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍሬው በቀለ እንደተናገሩት ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ በ19ኙ የምርጫ ክልሎች ሥር በሚገኙ 1 ሺህ 998 ጣቢያዎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ሲካሄድ ቆይቶ ማጠናቀቅ ተችሏል።

ትናንት ያልመረጡ ነዋሪዎች ቦርዱ በላከው የድምጽ መስጫ ወረቀት ዛሬ ድምጽ መስጠታቸውን አስታውቀዋል።

በአሁኑ ሰዓት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ ታዛቢዎች በተገኙበት ድምጽ የተሰጠባቸው ሳጥኖችን በማሸግ ለቆጠራ እየተዘጋጁ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።

በጣቢያዎቹ ሌሊቱን ቆጠራውን በማከናወን ውጤቱን ነገ ጠዋት ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግም አቶ ፍሬው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል የምርጫ ታዛቢ ቡድን ኢትዮጵያ ያካሄደችው ምርጫ የተረጋጋና ሰላማዊ ድባብ የተላበሰ መሆኑን እንደታዘበ ገለጸ።
Next articleቦርዱ ለክልሎችንና ከተማ አስተዳደሮች የምርጫ ቁሳቁስና ሰነዶች ከምርጫ ክልል ወደ አዲስአበባ በማጓጓዝ ሂደት ትብብር እንዲያደርጉለት ጠየቀ።