
በቤልጂየም፣ሉግዘምበርግ እና ሆላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የውጭ ጫናን የሚቃወም ሰልፍ አካሄዱ።
ባሕር ዳር: ሰኔ 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በቤልጂየም፣ ሉግዘምበርግና ሆላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ
ኢትዮጵያውያን በአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን በመገኘት በኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ያለውን ጫና በመቃወም ሰልፍ አካሂደዋል።
የሰልፉ አስተባባሪ የሆነው “ለኢትዮጵያ ዘብ እንቁም” አባላት ለአውሮፓ ኮሚሽንና ለአውሮፓ ምክር ቤት ያዘጋጁትንና ሕብረቱ
በኢትዮጵያ ላይ እያራመደ ባለው አቋም ላይ ያላቸውን ተቃውሞ የሚገልጽ ደብዳቤ ለሕብረቱ የዓለም ዓቀፍ ትብብር ቢሮና
የውጭ ጉዳይ ተወካዮች ማስረከባቸውን ከአስተባባሪዎቹ ያገኘነው መረጃ ጠቅሶ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ በማኅበራዊ
የትስስር ገጹ አመላክቷል።
ሰልፈኞቹ “በኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ጫናችሁን አቁሙ”፣ “የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትን አክብሩ”፣ “ዕውነትን እንጂ የፈጠራ ወሬዎችን
አትስሙ”፣ “ኢትዮጵያ ትቀጥላለች” እንዲሁም “በትግራይ ለተፈጠሩ ችግሮች ሁሉ መነሻ የሆነውን አሸባሪ ቡድን አውግዙ’
የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m