
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የሥራ ጉብኝት አካሄዱ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለሁለት ቀናት በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በነበራቸው ቆይታ ከሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ጋር ተገናኝተው መክረዋል።
የሁለቱ ሀገራትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንዲሁም በቀጣይ በተለያዩ ዘርፎች ሀገራቱ በሚኖራቸው ትብብር ዙሪያ መወያየታቸውን የምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
አቶ ደመቀ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የነበራቸውን የሥራ ተልዕኮ በማጠናቀቅ ወደ ሞስኮ – ሩሲያ አቅንተዋል ተብሏል።
አቶ ደመቀ ከሩሲያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
በሞስኮ በሚኖራቸው የሥራ ቆይታ ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለማስረዳት እና በሀገራቱ መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች የበለጠ ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡ መረጃው ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት የተገኘ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ