በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በአንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች ቆጠራዉ አሁንም እየተካሄደ ነው።

166
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በአንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች ቆጠራዉ አሁንም እየተካሄደ ነው።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 15/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ምሽት 3፡00 ምርጫዉ ሲጠናቀቅ ታዛቢ እና የመገናኛ ብዙኃን በተገኙበት ቆጠራ ተካሂዷል፡፡ በአንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች ቆጠራዉ አሁንም እየተካሄደ ነዉ።
የምርጫ ክልል 24 አስፈጻሚ ፋንታሁን አበራ ቆጠራ የጨረሱ ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስን ወደ ምርጫ ክልል እያስረከቡ እንደኾነ ለአሚኮ ገልጸዋል። የምርጫ አስተዳደር አካል ከምርጫ ጣቢያ ጀምሮ ያለዉን የምርጫ ዉጤት በቅብብሎሽ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንደሚያደርስም አቶ ፋንታሁን አብራርተዋል።
ጊዜያዊ የምርጫ ዉጤት በየምርጫ ጣቢያዉ ተለጥፏል፤ ጊዜያዊ ዉጤቱ ሲገለጽም የተመዘገበ ሕዝብ ብዛት፣ ጠቅላላ ድምጽ የሰጠ፣ ድምጽ ያልሰጠ መራጭ፣ የተበላሸ የድምጽ መስጫ ወረቀት፣ ዋጋ አልባ የድምጽ መስጫ ወረቀት ተብሎ መለየቱንም ነግረውናል።
ማንኛውም ቅሬታ ካለ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በየምርጫ ጣቢያዉም ስለሚገኝ ማቅረብ ይቻላልም ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ጺዮን አበበ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበስማዳ ምርጫ ክልል አንድ እና ሁለት ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶች በየምርጫ ጣቢያ እየተገለጸ ነው፡፡
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የሥራ ጉብኝት አካሄዱ፡፡