
“የምርጫው ውጤት በቦርዱ እስከሚገለፅ ተፎካካሪ ፓርቲዎች መግለጫ ከመስጠት ሊታቀቡ ይገባል” የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ድምፅ የመስጠት ሂደት እና ቆጠራ ተጠናቅቆ ውጤቱ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስከሚገለፅ ድረስ ተፎካካሪ ፓርቲዎች መግለጫ ከመስጠት እንዲታቀቡ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አሳስበ።
የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ዶክተር ራሔል ባፌ ምርጫውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ የምርጫው ውጤት በቦርዱ እስከሚገለጽ ድረስ ፓርቲዎች መግለጫ ከመስጠት እንዲታቀቡ ጠይቀዋል።
ቦርዱ ከፓርቲዎች እየቀረቡ ላሉ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ የመስጠት ሂደቱን ማጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል።
መራጮች ያደረጉትን ተሳትፎ ያደነቀው የጋራ ምክር ቤቱ፣ ሕዝቡ በቀጣይም ለሀገር ሰላም እና ደኅንነት በአንድነት እንዲቆም ጠይቋል።
መንግሥት የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት የማረጋገጡን ሥራ በትኩረት እንዲሠራም ማሳሰቡን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ