የምርጫ ሰዓት መራዘሙ ላልመረጡ ሰዎች ዕድል እንደሚሰጥ መራጮች ተናገሩ፡፡

125
የምርጫ ሰዓት መራዘሙ ላልመረጡ ሰዎች ዕድል እንደሚሰጥ መራጮች ተናገሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ምርጫ ክልል 24 ወረዳ 9 የምርጫ ጣቢያ 1እና2 እስከ ምሽት 3 ሰዓት ምርጫ መካሄድ በመቀጠሉ ያልመረጡ ዜጎች እንዲመርጡ እድል እንደሚሰጥ መራጮች ተናግረዋል።
ከምሽቱ 3 ሰዓት ምርጫዉ ሲጠናቀቅ ታዛቢ እና የመገናኛ ብዙኀን በተገኙበት ቆጠራ ይካሄዳል፡፡ ድምጽ በሚሰጥበት የምርጫ ጣቢያም ቆጠራዉ ይከናወናል። ቆጠራዉን በተገቢዉ ቅጻ ቅጽ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት ዉጤቱ ለሚመለከተዉ አካል ይተላለፋል፡፡ ነገ ጠዋትም በየምርጫ ጣቢያዉ ይፋ ይደረጋል።
የምርጫ አስተዳደር አካል ከምርጫ ጣቢያ ጀምሮ ያለዉን የምርጫ ዉጤት ቅብብል እስከ ማእከሉ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ያደርሳል። ዉጤት ሲገለጽም የተመዘገበ ሕዝብ ብዛት ጠቅላላ ድምጽ የሰጠ፣ ድምጽ ያልሰጠ መራጭ፣ የተበላሸ የድምጽ መስጫ ወረቀት፣ዋጋ አልባ የድምጽ መስጫ ወረቀት መካተት እንደሚኖርበት የምርጫ ቦርድ መረጃ ያመላክታል።
ማንኛውም ቅሬታ ካለ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በየምርጫ ጣቢያዉም ይገኛል።
ዘጋቢ፡- ጺዮን አበበ – ከኮልፌ ቀራንዮ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየባሕር ዳር ምርጫ ክልል የድምጽ መስጠት ሂደት ችግር አለማጋጠሙን የምርጫ ክልሉ አስተባባሪ ተናገሩ፡፡
Next articleበአዲስ አበባ በልደታ ክፍለ ከተማ የድምጽ አሰጣጡ እንደቀጠለ ነው፡፡